Interviews
Fana TV:
youtu.be/6xlJFDVWwhA
youtu.be/6xlJFDVWwhA
EBS TV:
youtu.be/xw3b4ZPGUJg
youtu.be/xw3b4ZPGUJg
የአባቶች ቀን በተለያዩ የአለም ሃገራት ቀን ተቆርጦለት በልዩ ልዩ ተግራት ይከበራል፤
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም መጋቢት ወር ላይ የአባቶች ቀን እንዲከበር ቀን ተቆርጦለታል፡፡ በኦስትሪያና ቤልጄም ደግሞ የሰኔ ወር 2ኛ እሁድ ላይ ዕለቱ ውሎ አባቶች እንዲመሰገኑ ተወስኗል፡፡ በተመሳሳይ በብራዚል የነሃሴ ወር 2ኛ እሁድ የአባቶች ቀን በልዩ ሁኔታ የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ከእነዚህ ሀገራት ባለፈ አብዛኞቹ ሀገራት የግንቦት ወር መጨረሻን ለአባቶች ቀን ሰጥተው ያከብራሉ፡፡ ሀገራቱ ከ5 አስርት አመታት በፊት አንስቶ እየተከበረ ዛሬን ድረስ ዘልቋል፡፡
በሃራችን ኢትዮጵያም ይሄው የአባቶች ቀን ተቆርጦለት መከበር ከጀመረ 13 ዓመታት ተቆጥሯል፤
በእነዚህ አመታት በየቦታው በልዩ ልዩ ሁኔታ እና ህይወት ውስጥ የሚገኙ አባቶችን በጋራም በተናጥልም እግር ከማጠብ እስከ ጋቢ ማልበስ የዘለቀ የክብር ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
“የአባቶች ቀን” በሚል የጀመረው እለቱ አሁን “የኢትዮጵያ የአባቶች ቀን” የሚል ስያሜን አግኝቷል፡፡
ይህ ዕለት የተመረጠበት ዋነኛ ምክንያት ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት የተዋደቁ ጀግኖች አባቶቻችንን ለማሰብ ነው፡፡
ግንቦት 15 1888 ጀግኖች አባቶቻችን ጣልያንን ድል አድርገው ከወራት ዘመቻ በኃላ ተመልሰው ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ዕለት ነው፡፡
ይሄው ዕለትም ጀግኖች አባቶቻችን ለኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራን በመፈንጠቅ፣ ጥቁሮች በነጮች መደፈር ሳይሆን ጥቁሮችም ነጮችን ማሸነፍ እንደሚችሉ ያስመሰከሩበት ነው፡፡
ይሄንኑ ታሪክ ጠብቆ ለማቆየት ብሎም ለሃገር የተዋደቁ፣ ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ለመላው አለም ህዝብ ተዓምራዊ የተባለለትን ታሪክን የፈፀሙ አባቶችን በማሰብ ዕለቱ ግንቦት 15 እንዲሆን ተሰይሟል፡፡